Posts

Image
ከቀን ቅዱስ ሃሙስ ከስም ልዩ ቴዎድሮስ ፨፨፨ አፄ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ― የኢትዮጵያ ንጉስ፣ ዘመነመሳፍንትን ቀብረው ኢትዮጵያን እንደገና ያዋሃዱ፣ ከተራ ሽፍታነት ተነስተው የታላቅ ሃገር ንጉስ የሆኑ፣ የጦር ስልት አዋቂ ቴዎድሮስ አድኃኖም ― ከአንድ ሃገር የክልል ጤና ቢሮ ተነስተው፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ብሎም የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑ ቴዎድሮስ ገብሬ ― ስነፅሁፍን ሳይንሳዊ በሆነ መልክ የሚተነትን ድንቅ ኢትዮጵያዊ ሃያሲ፣ ታላላቅ የሂስ ስራዎቹ ያነበብነውን ባላየነው አቅጣጫ የሚከስትልን ቴዎድሮስ ታደሰ ― አስደናቂ ድምፃዊ። ከኢትዮጵያ ወርቃማ የሙዚቃ ዘመን ከታላላቆቹ ሙዚቀኞች አንዱ ቴዎድሮስ ካሳሁን ―ከዘመናችን ድምፃውያን አንዱ። ከድምፁ ባሻገር የግጥምና ዜማ ጠቢብ ቴዎዶር ሩዝቬልት ― የአሜሪካ ፕሬዚዳንት  ቴዎድሮስ ምትኩ — ቴዲ ምትኩ ኢንስትሩመንታል (በተለምዶ የአየር መንገድ ክላሲካል)የተጫወተ ጉምቱ ሳክስፎኒስት ነው። እንደዛሬ ማንም እየተነሳ ሳክስ ሳይነፋ በፊት ቴዲ ከሶል ኤኮስ(ከወንድሙ ከተሾመ ምትኩ ጋር) እስከ ደመራና ሌሎችም ባንዶች በግል ከሙላቱ ከጥላሁን እና ከሌሎች እውቆች ጋር ሰርቷል!ቴዲ በኔ ብያኔ ከያሬድ ተፈራም ሆነ ከጌታቸው መኩሪያ እኩል የሚቀመጥ ባለሙያ ነው። ቴዎድሮስ መኮንን(ቴዲ-ማክ)—የታዋቂው አብራሪ ካፒቴን መኮንን በሪ ልጅ ነው። ግን ቴዲ ከዚያም በላይ ነው። የራሱን መንገድ ቀይሶ ከታላላቆቹ የኢትዮጵያ የሙዚቃ አቀናባሪዎች ከነ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ጋር የሚመደብ ሙዚቀኛ ነው። ብዙ የሙዚቃ አልበሞች ቢያቀናብርም ማስተርፒሱ የአስቴር አወቀ ኤቦ አልበም ነው። ከዚህ ባሻገር በኢትዮጵያ አይዶል ተወዳዳሪ የነበረችው የታዳጊዋን ሃና የኦፔራ ሙዚቃ ተሰጥኦ በመመልከት ባለው ጥልቅ የሙዚቃ እውቀት...

"እብዱ" አውግቸው

Image
 ሕሩይ ሚናስ እውነተኛ ስሙ ነው - የሚታወቀው ግን ራሱ ለራሱ እና ለኣባቱ ጭምር ባወጣው ስም ነው። ሕሩይ አንድ ወቅት ላይ አበደ! ሁናቴውን ተናፋቂው ኮከብ ጋሽ ኃይለመለኮት እንዲህ ያወሳዋል።  ★በዚያች የንባ ብ ቤት ስመላለስ ከአቀማመጥ ጀምሮ በመልክ ጭምር የሚመሳሰሉት ጋሽ ስብሐት ለኣብ እና እርሱ ያላቸውን ፍቅር እና ከበሬታ ስለማውቅ፥ የእርሱን ማበድ ስሰማ ለጋሽ ስብሐት በጣም ደነገጥኩ። ጭራሽ ደግሞ ሕሩይ ሸሚዙን ቀዶ ሲሮጥ፣ ከራሱ ጋር ሲለፈልፍ አየሁት፥ ወደዚያች የጥበብ ቤታችን ሄድኩ፥ እንዳሰብኩትም ሚናስ ባይኖርም ጋሽ ስብሐት መጽሐፍ ይዞ ሚናስ ቤት ተቀምጧል። እንዴት እንደምጀምር ስፈራ ስቸር ቆይቼ  ... "ጋሽ ስብሐት፥ ሕሩይ እኮ አበደ!" አልኩት። የሚያሳየውን የአካል ለውጥ ስጠብቅ ጋሽ ስብሐት ሳይሞቀውም፣ ሳይበርደውም ስመለከት ከእኔ ቀድሞ የነገረው ሰው ይኖራል ብዬ አሰብኩ፥ ወዲያው ግን ጋሽ ስብሐት ካቀረቀረበትም ቀና ሳይል፦ "ደግ፣ እሰይ" አለኝ ጭራሽ ምንም ሳይመስለው።  "ጋሽ ስብሐት ሰምተኸኛል? ሕሩይ አበደ፣ ጨርቁን ጣለ፣ ብቻውን መንገድ ለመንገድ እየጮኸ አየሁት ነው እኮ የምልህ" አልኩት።  "እንኳን፣ እሰይ" አለኝ በድጋሚ።  "ምነው? ለምን?" ብለው። "በቃ  ተገላገለ፥ ነፃ ወጣ!" አለኝ።★  ሲል ሲያወራ ቢውል በሚያስመኝ አንደበቱ ወቅቱን ይገልፀዋል።  ሕሩይ በበኩሉ በዚያ የ"እብደት" ጊዜው ውስጥ ሳለ ያየውን፣ ድንገት በሕሊናው ይከሰት የነበረውን፣ የእብደት ዓለም አስተሳሰብ "እብዱ" በሚል ርዕስ ከትቦ ለንባብ አበቃው።  ሕሩይ ሚናስ - ወይም ራሱ ለራሱ ባወጣው ስም ደግሞ ኣውግቸው ተረፈ!  ረዥም እድሜ ከ...